የቁም ቅዠት

የቀኝ እጅ ፀሐፊ ነኝ። እናም እየፃፍኩ ነው - በሙሉ ጥበባዊ ስሜት። እየፃፍኩ እያለ ከቀኝ እጄ ብብት አካባቢ ኃይል ያለው ሙቀት ተሰማኝ። ‹ዛሬ እውነትም እየፃፍኩ ነው!› አልኩኝ - ለራሴ። ሙቀቱ ኃይሉን ጨምሮ ይሞቃል - ከዛው ከብብቴ። ከዚህ ቀደም ተሰምቶኝ የማያውቅ፣ ለየት ያለ እርጥበት ሁሉ ይሰማኝ ጀምሯል። እናም ከላይ የደረብኩትን ጃኬት አወለኩት። ኡፍፍ… አሁን ሙቀቱ እየቀነሰ ነው፤ …

Advertisements

ቁልፍ ይዞ ማንኳኳት

ነፋሱ በተጨነቀ ድምፅ ይጮኻል፡፡ እሱ ጮኾ ዛፎቹን ያስጨንቃቸዋል፤ ከወዲያ ወዲህ ያንገላታቸዋል፡፡ በነፋሱ ለቅሶ፣ በዛፎቹ ሁካታ ፀጥታው የተረበሸው ጨለማ ለነፋስ እንዲህ አለው፣ “ምን ሆነኻል? መኝታዬ ላይስ እሾህ የምትነሰንሰው ለምንድነው? ስለምንስ ዝምታዬን እንዳልሰማ ታደርጋለህ?” ነፋስም ለአንድ አፍታ ቆም ብሎ ጨለማን ተመለከተው፡፡ የባዶነት ግርማ ሞገሱ ቢያስፈራውም ሀሳቡን ለመንቀፍ ወደኋላ አላለም፡፡ “ታዲያ እንዳንተ ‘የሆነውንም ሆኖ፣ የሚሆነውንም እንዲሆን የሚፈቅድ’ መሆን …

ነፃ-ፈቃድ (FREEWILL)

ኑሮዋ ባለመሳካቱ መሳካቱን የምታምን ሴት ብትኖር እናቴ ብቻ ናት፡፡ የለፋችበት ሁሉ ሳይሆንላት ሲቀር፣ “አለፋፌም እኮ እንዳይሆን ነበር፤ ስለዚህ ሆኖልኛል ማለት ነው!” በማለት እራሷን የምታፅናና፣ በመፅናናቷም የደስታ ደሴት ላይ ተቀምጣ የሐሴት ባህርን እየጠለቀች የኑሮ ጥማቷን የምታረካ ብልህ ሴት፡፡ ‹ተመስጌን› ማለትን እንደመተንፈስ አምና የተቀበለችው እናቴ ሁሌም ቢሆን ዛሬን እንዳትራብ ነው ጥረቷ፡፡ በደሴቷ ላይ እየኖረ ደሴቷን የፈጠራት ባህር …

በእጅ የያዙት. . .

“ጥርስሽ እንደማታ ጀንበር የውበት ብርሃኑን የሚያፈናጥቀው ተፈጥሮ በስጦታ መልክ ያበረከተችልሽ ውበት እንዳይመስልሽ -- መስተዋት ብቻ የሆነው ጥርስሽ የእኔን ወርቃማነት ሲያንፀባርቅ እንጂ! “ትወጂኛለሽ፣ ደስታን ከእኔ እንጂ በውልደት አላገኘሽውም፡፡ ባየሽኝ ጊዜ በባዶነት የተሞላው ውስጥሽ በጥርስሽ ፈገግ ማለት ብቻ ደስታን መሰብሰብ ይጀምራል፡፡ ፈገግታሽ ያምራል፤ ማማሩ ግን የእኔው ውጤት ነው፤ ከእኔው የመጣ ውበት፡፡ “ለማየት ብቻ የተፈጠረው … ያ እንኳን …

“የትየለሌዎቹ”

እነዚያን የለሰለሱ ጉንጮቿን እንድዳብሳቸው ይጠቁመኝና የጨበጥኩትን ቦክስ እንድፈታ ያደርገኛል፡፡ ኋላ መሀሉ ላይ ስርጉድ ያለበትን የግራ ጉንጯን ብዬ ቀኝ እጄን ብሰድ … “የምን መዳበስ ነው… በጥፊ በላት እንጂ!!” ሲለኝ ክው እላለሁ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አፌን አሞጥሙጬ የስድቡን ናዳ ላወርድባት ስቃጣ… “ተው እንጂ ተረጋጋ፣ እነዚህ የሚበሉ ከንፈሮቿን ተመገባቸው” ይለኛል፡፡ እኔም የእርሱን ምክር መስማት አያርመኝ ከንፈሮቼን አሹዬ ከከንፈሮቿ …