የቁም ቅዠት

የቀኝ እጅ ፀሐፊ ነኝ። እናም እየፃፍኩ ነው - በሙሉ ጥበባዊ ስሜት። እየፃፍኩ እያለ ከቀኝ እጄ ብብት አካባቢ ኃይል ያለው ሙቀት ተሰማኝ። ‹ዛሬ እውነትም እየፃፍኩ ነው!› አልኩኝ - ለራሴ። ሙቀቱ ኃይሉን ጨምሮ ይሞቃል - ከዛው ከብብቴ። ከዚህ ቀደም ተሰምቶኝ የማያውቅ፣ ለየት ያለ እርጥበት ሁሉ ይሰማኝ ጀምሯል። እናም ከላይ የደረብኩትን ጃኬት አወለኩት። ኡፍፍ… አሁን ሙቀቱ እየቀነሰ ነው፤ …

Advertisements

ሀገር ማስፈራሪያ

ከሰሃራ በታች - በምስራቅ አፍሪካ ከስዋ'ሚስተካከል - ጫፍዋን የሚነካ ከቶ'ልተፈጠረም ነፍሴን የሚያፈካ፡፡ «ምነው በሰሜንስ - በምራብ፣ በደቡብ ኤሮጵ አሜሪካ - ኤስያና አረብ ሞልትዋል ማለትህ ነው ከጫፌ'ሚቀርብ?» ብላ እንዳጠይቀኝ - እኔ መልስ የለኝም ሳቅዋ ይበቃኛል - ሌላ'ይስማማኝም፤ ግና ሆነ ብዬ - ሀገር ማስተረፌ ሀጉር መደበቄ - ካርታ ማስቀረቴ አያድርሰውና ያኮረፈች ጊዜ ቁጣ-ቁጣ ብልዋት የነደዳት ጊዜ ልብ-ልብ …

ና በይኝ

ና በይኝ አሁን - እመጣለሁ ዝም ካልሽማ - እዘገያለሁ ደርሶ ፈርዶብኝ - ሰው እሰማለሁ፡፡ «ሳቅዋ አይሰማ - ጨልምዋል ቤቱ እስዋ ተሌለች - የታል ሙቀቱ ቢቀር ይሻል የል - ተመሸበቱ፡፡» ይላል ጎረቤት - ይሰዳል ወሬ እኔም ለምዶብኝ - ሰማሁ ታትሬ፡፡ ሚያዚያ 10፣2010

ባለንብረት

አንቺ ጋ ነው'ንጂ የት እሆናለሁኝ አንቺ ጋር ነው እንጂ የት እስቃለሁኝ አንቺ ፊት ነው እንጂ የት አወልቃለሁኝ የሚለውን ባል ነው ተጠንቀቂ ያልኩት ቆፍጠን በይ እህት ፊትሽን ሰስቺበት ፊት ያገኘ ለታ፣ አንቺ ላይ ካልጮህኩኝ - የት ሄጄ ልጩህ ነው አንቺን ካልመታሁኝ - ማን ሊመታልኝ ነው ማለቱ አይቀርም ፍቅር-ገፊ ባልሽ ስታስተዋውቂው «ባለቤቴ» ብለሽ ከውነት ቆጥሮት ኖርዋል ንብረቱ …

ቅዱስ ቶማስ አኩዊናስ (1225-74)

ቅዱስ ቶማስ የተወለደው በጣሊያን አኩዊኖ አቅራቢያ፣ በሮካሲካ ቤተ-ነገሥት (Castle) ውስጥ፣ ከባለፀጋና ከመኩዋንንት ቤተሰብ ነበር፡፡ ትምህርት የጀመረውም አጎቱ የበላይ ኃላፊ በነበሩበት ቤኔዲክታዊ (ቅዱስ ቤኔዲክት በመሠረተው ሥርዓት በሚመራው) የሞንቴ ካሲኖ   ገዳም ውስጥ ነው፡፡ ዕድሜው ሃያ እንደደረሰ፣ ከቤተሰቦቹ ተቃውሞ እየገጠመው ቢሆንም፣ በቅዱስ ዶሚኒክ የተፀነሰውን የሮማ ካቶሊክ ዶሚኒካን ሥርዓት ተቀላቀለ፤ እንዲሁም ከጀርመናዊው የሃይማኖት አስምህሮ ልሂቅ፣ ከአልቤርተስ ማግነስ እውቀትን ለመቅሰም …

ቅዱስ ኦገስቲን (354-430)

ኦገስቲን የተወለደው አልጄሪያ ውስጥ ነው፤ ቀድሞ ታኽገስቴ፣ አሁን ደግሞ ሱክ አኽራስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ፡፡ እናቱ ክርስቲያን ብትሆንም ወደ እምነቱ እንዲጠጋ ለምታደርጋቸው ጥረቶች ምላሽ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ወጣት ሳለ የሲስሮ እና የፕሎቲነስ አድናቂ የነበረ ሲሆን “ማንቼይዝም” ለተባለው (Manichaeism - የክርስትና እና የባዕድ እምነቶች አለባዊያንን ያካተተ) የሃይማኖት ሥርዓት እና ለስኬፕቲሲዝም (የጠርጣራነት ፍልስፍና) ትኩረት ነበረው፡፡ የእርሱ የበሰለ ምሁራዊ አቋም …

ሲስሮ (106-43 ዓ.ዓ)

ማርከስ ቱሊየስ ሲስሮ ከመኳንንት ባይሆንም ከባለፀጋ ቤተሰብ በአርፒነም፣ በ106 ዓ.ዓ ነው የተወለደው፡፡ በ75 ዓ.ዓ በምዕራብ ሲሲሊ የገቢዎች ሹም ሆኖ አገልግሏል፤ በኋላም በቀድሞዋ ሮም ሪፐብሊክ በሕዝብ ዘንድ ግዙፍ ቦታ የሚሰጠውና የተናገረው ሁሉ አድማጭን ከማሳመን በቀር መሬት ጠብ የማይልበት አንደበተ-ርቱ (orator) ለመሆን በቅቷል፡፡ የሲሲሊ አገረ ገዥ የነበረውን ጃየስ ቬሬስ (በ70 ዓ.ዓ) ሕግ ፊት በማቆም ያስመዘገበው ስኬት፣ እንዲሁም …